ዘፍጥረት 18:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ጩኸት በእርግጥም ታላቅ ነው፤+ ኃጢአታቸውም እጅግ ከባድ ሆኗል።+ ዘዳግም 32:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ወይናቸው ከሰዶም የወይን ተክልናከገሞራ የእርሻ ቦታ የተገኘ ነው።+ የወይን ፍሬያቸው መርዛማ የወይን ፍሬ ነው፤ዘለላቸው መራራ ነው።+ ኢሳይያስ 1:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እናንተ የሰዶም+ አምባገነኖች፣* የይሖዋን ቃል ስሙ። እናንተ የገሞራ+ ሰዎች፣ የአምላካችንን ሕግ* አዳምጡ። ይሁዳ 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በተመሳሳይም ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በዙሪያቸው የነበሩ ከተሞች ራሳቸውን ልቅ ለሆነ የፆታ ብልግና* አሳልፈው የሰጡ ከመሆኑም ሌላ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሥጋ ፍላጎታቸውን ያሳድዱ ነበር፤+ በመሆኑም በዘላለም እሳት ፍርድ ተቀጥተው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆነዋል።+
7 በተመሳሳይም ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በዙሪያቸው የነበሩ ከተሞች ራሳቸውን ልቅ ለሆነ የፆታ ብልግና* አሳልፈው የሰጡ ከመሆኑም ሌላ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሥጋ ፍላጎታቸውን ያሳድዱ ነበር፤+ በመሆኑም በዘላለም እሳት ፍርድ ተቀጥተው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆነዋል።+