ዘዳግም 30:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በሕይወትም ትኖር ዘንድ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ* እንድትወደው+ አምላክህ ይሖዋ ልብህን እንዲሁም የልጆችህን ልብ ያነጻል።*+ ኤርምያስ 31:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 “ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና” ይላል ይሖዋ። “ሕጌን በውስጣቸው አኖራለሁ፤+ በልባቸውም እጽፈዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+ ሕዝቅኤል 11:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እኔም አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤+ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አኖራለሁ፤+ ድንጋይ የሆነውንም ልብ ከሰውነታቸው አውጥቼ+ የሥጋ ልብ* እሰጣቸዋለሁ፤+
33 “ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና” ይላል ይሖዋ። “ሕጌን በውስጣቸው አኖራለሁ፤+ በልባቸውም እጽፈዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+