2 ነገሥት 22:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ከዚያም ንጉሡ ካህኑን ኬልቅያስን፣ የሳፋንን ልጅ አኪቃምን፣+ የሚካያህን ልጅ አክቦርን፣ ጸሐፊውን ሳፋንን እና የንጉሡን አገልጋይ አሳያህን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 13 “ሄዳችሁ በተገኘው በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን ቃል በተመለከተ እኔን፣ ሕዝቡንና መላውን ይሁዳ ወክላችሁ ይሖዋን ጠይቁ፤ ምክንያቱም አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ ላይ እኛን አስመልክቶ የሰፈረውን ቃል ስላልታዘዙ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በእኛ ላይ ነዷል።”+ ኤርምያስ 39:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በመሆኑም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን፣ ራብሳሪስ* የሆነው ናቡሻዝባን፣ ራብማግ* የሆነው ኔርጋልሻሬጸር እንዲሁም የባቢሎን ንጉሥ ሹማምንት ሁሉ ልከው 14 ኤርምያስን ከክብር ዘቦቹ ግቢ+ አስወጡት፤ ደግሞም ወደ ቤቱ እንዲወስደው ለሳፋን+ ልጅ፣ ለአኪቃም+ ልጅ፣ ለጎዶልያስ+ ሰጡት። በመሆኑም ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ተቀመጠ። ኤርምያስ 40:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ኤርምያስ ከመመለሱ በፊት ናቡዛራዳን እንዲህ አለው፦ “የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን+ ልጅ፣ ወደ አኪቃም+ ልጅ ወደ ጎዶልያስ+ ተመለስ፤ በሕዝቡም መካከል ከእሱ ጋር ተቀመጥ፤ ወይም ደግሞ ወደመረጥከው ቦታ ሂድ።” ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው።
12 ከዚያም ንጉሡ ካህኑን ኬልቅያስን፣ የሳፋንን ልጅ አኪቃምን፣+ የሚካያህን ልጅ አክቦርን፣ ጸሐፊውን ሳፋንን እና የንጉሡን አገልጋይ አሳያህን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 13 “ሄዳችሁ በተገኘው በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን ቃል በተመለከተ እኔን፣ ሕዝቡንና መላውን ይሁዳ ወክላችሁ ይሖዋን ጠይቁ፤ ምክንያቱም አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ ላይ እኛን አስመልክቶ የሰፈረውን ቃል ስላልታዘዙ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በእኛ ላይ ነዷል።”+
13 በመሆኑም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን፣ ራብሳሪስ* የሆነው ናቡሻዝባን፣ ራብማግ* የሆነው ኔርጋልሻሬጸር እንዲሁም የባቢሎን ንጉሥ ሹማምንት ሁሉ ልከው 14 ኤርምያስን ከክብር ዘቦቹ ግቢ+ አስወጡት፤ ደግሞም ወደ ቤቱ እንዲወስደው ለሳፋን+ ልጅ፣ ለአኪቃም+ ልጅ፣ ለጎዶልያስ+ ሰጡት። በመሆኑም ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ተቀመጠ።
5 ኤርምያስ ከመመለሱ በፊት ናቡዛራዳን እንዲህ አለው፦ “የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን+ ልጅ፣ ወደ አኪቃም+ ልጅ ወደ ጎዶልያስ+ ተመለስ፤ በሕዝቡም መካከል ከእሱ ጋር ተቀመጥ፤ ወይም ደግሞ ወደመረጥከው ቦታ ሂድ።” ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው።