2 ነገሥት 25:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በተጨማሪም የዘቦቹ አለቃ የካህናት አለቃ የሆነውን ሰራያህን፣+ ሁለተኛውን ካህን ሶፎንያስንና+ ሦስቱን የበር ጠባቂዎች ወሰዳቸው።+ 2 ነገሥት 25:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 የባቢሎን ንጉሥ በሃማት+ ምድር ባለችው በሪብላ ሰዎቹን መትቶ ገደላቸው። በዚህ መንገድ ይሁዳ ከምድሩ በግዞት ተወሰደ።+ ኤርምያስ 21:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ንጉሥ ሴዴቅያስ+ የማልኪያህን ልጅ ጳስኮርንና+ የማአሴያህን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን+ ወደ ኤርምያስ በላካቸው ጊዜ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ እነሱም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ 2 “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ሊወጋን ስለሆነ+ እባክህ፣ ስለ እኛ ይሖዋን ጠይቅልን። ንጉሡ ከእኛ እንዲመለስ ይሖዋ እንደቀድሞው ሁሉ አሁንም ተአምር ይፈጽምልን ይሆናል።”+ ኤርምያስ 37:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ንጉሥ ሴዴቅያስም የሸሌምያህን ልጅ የሁካልንና+ የካህኑን የማአሴያህን ልጅ ሶፎንያስን+ “እባክህ፣ ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ጸልይ” ብለው እንዲነግሩት ወደ ነቢዩ ኤርምያስ ላካቸው። ኤርምያስ 52:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 በተጨማሪም የዘቦቹ አለቃ የካህናት አለቃ የሆነውን ሰራያህን፣+ ሁለተኛውን ካህን ሶፎንያስንና+ ሦስቱን የበር ጠባቂዎች ወሰዳቸው።+ ኤርምያስ 52:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 የባቢሎን ንጉሥ በሃማት ምድር ባለችው በሪብላ+ ሰዎቹን መትቶ ገደላቸው። በዚህ መንገድ ይሁዳ ከምድሩ በግዞት ተወሰደ።+
21 ንጉሥ ሴዴቅያስ+ የማልኪያህን ልጅ ጳስኮርንና+ የማአሴያህን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን+ ወደ ኤርምያስ በላካቸው ጊዜ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ እነሱም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ 2 “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* ሊወጋን ስለሆነ+ እባክህ፣ ስለ እኛ ይሖዋን ጠይቅልን። ንጉሡ ከእኛ እንዲመለስ ይሖዋ እንደቀድሞው ሁሉ አሁንም ተአምር ይፈጽምልን ይሆናል።”+
3 ንጉሥ ሴዴቅያስም የሸሌምያህን ልጅ የሁካልንና+ የካህኑን የማአሴያህን ልጅ ሶፎንያስን+ “እባክህ፣ ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ጸልይ” ብለው እንዲነግሩት ወደ ነቢዩ ኤርምያስ ላካቸው።