16 ከዚያም ሄሮድስ ኮከብ ቆጣሪዎቹ እንዳታለሉት ሲያውቅ በጣም ተናደደ፤ ኮከቡ የታየበትን ጊዜ በተመለከተ ከኮከብ ቆጣሪዎቹ ባገኘው መረጃ መሠረት+ ሰዎች ልኮ በቤተልሔምና በአካባቢዋ ሁሉ የሚገኙትን ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑትን ወንዶች ልጆች በሙሉ አስገደለ። 17 በዚህ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው የሚከተለው ቃል ተፈጸመ፦ 18 “የለቅሶና የዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ። ራሔል+ ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ ልጆቿ ስለሌሉ ልትጽናና አልቻለችም።”+