-
ኤርምያስ 50:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 “በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣
“የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤
ሆኖም አይገኝም፤
የይሁዳም ኃጢአት አይገኝም፤
እንዲተርፉ ያደረግኳቸውን ይቅር እላቸዋለሁና።”+
-
-
ዕብራውያን 8:10-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 “‘ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና’ ይላል ይሖዋ።* ‘ሕግጋቴን በአእምሯቸው ውስጥ አኖራለሁ፤ በልባቸውም ላይ እጽፋቸዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።+
11 “‘እነሱም እያንዳንዳቸው የአገራቸውን ሰው፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን “ይሖዋን* እወቅ!” ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም። ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና። 12 ለክፉ ሥራቸው ምሕረት አደርግላቸዋለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም።’”+
-
-
ዕብራውያን 10:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 በመቀጠልም “ኃጢአታቸውንና የዓመፅ ድርጊታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም” ይላል።+
-