ዘዳግም 4:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 “እዚያ ሆናችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ብትፈልጉት፣ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ብትሹት በእርግጥ ታገኙታላችሁ።+ 2 ዜና መዋዕል 7:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በስሜ የተጠሩትም ሕዝቤ+ ራሳቸውን ዝቅ ቢያደርጉ፣+ ቢጸልዩ፣ ፊቴን ቢሹና ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ፣+ ከሰማያት ሆኜ እሰማለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።+ 2 ዜና መዋዕል 34:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ስለዚህ ቦታና ስለ ነዋሪዎቹ የተናገረውን ቃል ስትሰማ ልብህ ስለተነካና* በአምላክ ፊት ራስህን ስላዋረድክ እንዲሁም ራስህን በፊቴ ዝቅ ስላደረግክ፣ ልብስህን ስለቀደድክና በፊቴ ስላለቀስክ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል ይሖዋ።+
14 በስሜ የተጠሩትም ሕዝቤ+ ራሳቸውን ዝቅ ቢያደርጉ፣+ ቢጸልዩ፣ ፊቴን ቢሹና ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ፣+ ከሰማያት ሆኜ እሰማለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።+
27 ስለዚህ ቦታና ስለ ነዋሪዎቹ የተናገረውን ቃል ስትሰማ ልብህ ስለተነካና* በአምላክ ፊት ራስህን ስላዋረድክ እንዲሁም ራስህን በፊቴ ዝቅ ስላደረግክ፣ ልብስህን ስለቀደድክና በፊቴ ስላለቀስክ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል ይሖዋ።+