14 ኢየሩሳሌምን በሙሉ፣ መኳንንቱን በሙሉ፣+ ኃያላን ተዋጊዎቹን ሁሉ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን+ በአጠቃላይ 10,000 ሰዎችን በግዞት ወሰደ። በጣም ድሃ ከሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች በስተቀር በዚያ የቀረ አልነበረም።+ 15 በዚህ መንገድ ዮአኪንን+ ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤+ በተጨማሪም የንጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።