ሕዝቅኤል 25:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በእጅህ ስላጨበጨብክና+ በእግርህ መሬቱን ስለመታህ እንዲሁም በእስራኤል ምድር ላይ የደረሰውን ሁኔታ ስታይ በንቀት ተሞልተህ* ሐሴት ስላደረግክ፣+ 7 ብሔራት እንዲበዘብዙህ ለእነሱ አሳልፌ እሰጥህ ዘንድ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ። ከሕዝቦች መካከል አስወግድሃለሁ፤ ከአገራትም መካከል ለይቼ አጠፋሃለሁ።+ እደመስስሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ።’ አብድዩ 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በወንድምህ ቀን ይኸውም ወንድምህ ክፉ ነገር በደረሰበት ቀን መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤+የይሁዳ ሕዝብ በጠፋበት ቀን ሐሴት ማድረግ አልነበረብህም፤+ደግሞም በጭንቀታቸው ቀን በእብሪት መናገር አይገባህም ነበር።
6 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በእጅህ ስላጨበጨብክና+ በእግርህ መሬቱን ስለመታህ እንዲሁም በእስራኤል ምድር ላይ የደረሰውን ሁኔታ ስታይ በንቀት ተሞልተህ* ሐሴት ስላደረግክ፣+ 7 ብሔራት እንዲበዘብዙህ ለእነሱ አሳልፌ እሰጥህ ዘንድ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ። ከሕዝቦች መካከል አስወግድሃለሁ፤ ከአገራትም መካከል ለይቼ አጠፋሃለሁ።+ እደመስስሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ።’
12 በወንድምህ ቀን ይኸውም ወንድምህ ክፉ ነገር በደረሰበት ቀን መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤+የይሁዳ ሕዝብ በጠፋበት ቀን ሐሴት ማድረግ አልነበረብህም፤+ደግሞም በጭንቀታቸው ቀን በእብሪት መናገር አይገባህም ነበር።