ኤርምያስ 13:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እነሱንም እርስ በርሳቸው፣ አባቶችንና ልጆችንም አጋጫለሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ምንም ዓይነት ርኅራኄም ሆነ አዘኔታ አላሳይም፤ ምሕረትም አላደርግላቸውም፤ እነሱን ከማጥፋት ምንም ነገር አያግደኝም።”’+ ኤርምያስ 21:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “‘“ከዚያም በኋላ” ይላል ይሖዋ፣ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣ አገልጋዮቹን እንዲሁም ከቸነፈር፣ ከሰይፍና ከረሃብ ተርፎ በከተማዋ ውስጥ የሚቀረውን ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ፣ በጠላቶቻቸው እጅና ሕይወታቸውን ለማጥፋት በሚሹ* ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ እሱም በሰይፍ ይመታቸዋል። አያዝንላቸውም፤ ርኅራኄም ሆነ ምሕረት አያሳያቸውም።”’+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:43 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 ጨርሶ እንዳንቀርብ በቁጣ አገድከን፤+አሳደድከን፤ ያለርኅራኄም ገደልከን።+ ሕዝቅኤል 5:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በአስጸያፊ ጣዖቶችሽ ሁሉና ጸያፍ በሆኑ ድርጊቶችሽ ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፣+ እኔ ራሴ እተውሻለሁ፤* ዓይኔ አያዝንም ደግሞም አልራራም።+ ሕዝቅኤል 9:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ሽማግሌውን፣ ወጣቱን፣ ድንግሊቱን፣ ሕፃኑንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ።+ ምልክቱ ወዳለበት ወደ ማንኛውም ሰው ግን አትቅረቡ።+ ከመቅደሴም ጀምሩ።”+ ስለዚህ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት በነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።+
14 እነሱንም እርስ በርሳቸው፣ አባቶችንና ልጆችንም አጋጫለሁ” ይላል ይሖዋ።+ “ምንም ዓይነት ርኅራኄም ሆነ አዘኔታ አላሳይም፤ ምሕረትም አላደርግላቸውም፤ እነሱን ከማጥፋት ምንም ነገር አያግደኝም።”’+
7 “‘“ከዚያም በኋላ” ይላል ይሖዋ፣ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣ አገልጋዮቹን እንዲሁም ከቸነፈር፣ ከሰይፍና ከረሃብ ተርፎ በከተማዋ ውስጥ የሚቀረውን ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር* እጅ፣ በጠላቶቻቸው እጅና ሕይወታቸውን ለማጥፋት በሚሹ* ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ እሱም በሰይፍ ይመታቸዋል። አያዝንላቸውም፤ ርኅራኄም ሆነ ምሕረት አያሳያቸውም።”’+
11 “‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በአስጸያፊ ጣዖቶችሽ ሁሉና ጸያፍ በሆኑ ድርጊቶችሽ ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፣+ እኔ ራሴ እተውሻለሁ፤* ዓይኔ አያዝንም ደግሞም አልራራም።+
6 ሽማግሌውን፣ ወጣቱን፣ ድንግሊቱን፣ ሕፃኑንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ።+ ምልክቱ ወዳለበት ወደ ማንኛውም ሰው ግን አትቅረቡ።+ ከመቅደሴም ጀምሩ።”+ ስለዚህ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት በነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።+