ኤርምያስ 3:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት አብረው ይሄዳሉ፤+ በአንድነት ከሰሜን ምድር ተነስተው ለአባቶቻችሁ ርስት አድርጌ ወደሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።+ ሆሴዕ 1:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ተሰብስበው አንድ ይሆናሉ፤+ ለራሳቸውም አንድ መሪ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።+