-
2 ነገሥት 19:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ሕዝቅያስ ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ ያቀረብከውን ጸሎት ሰምቻለሁ።+
-
-
ሕዝቅኤል 29:3, 4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
አንተ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት፣ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን፣ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ።+
4 በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፤ በአባይ ወንዝህ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ከቅርፊትህ ጋር እንዲጣበቁ አደርጋለሁ።
ቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁት የአባይ ዓሣዎች ሁሉ ጋር ከአባይ ወንዝህ መካከል አወጣሃለሁ።
-
-
ሕዝቅኤል 39:2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 እመልስሃለሁ፤ ደግሞም እነዳሃለሁ፤ ራቅ ካለውም የሰሜን ምድር አምጥቼ+ ወደ እስራኤል ተራሮች እወስድሃለሁ።
-