-
ዘፀአት 40:29አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት የሚቃጠለውን መባና የእህሉን መባ በላዩ ላይ እንዲያቀርብበት የሚቃጠል መባ የሚቀርብበትን መሠዊያ+ በማደሪያ ድንኳኑ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ አደረገው።
-
-
ዘሌዋውያን 8:18-21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 እሱም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ጫኑ።+ 19 ከዚያም ሙሴ አውራውን በግ አረደው፤ ደሙንም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። 20 አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራረጠው፤ ቀጥሎም ጭንቅላቱን፣ ብልቶቹንና ሞራውን* አጨሰው። 21 ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠባቸው፤ ሙሴም አውራው በግ በሙሉ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። ይህም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ ነበር። ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነበር።
-
-
ሕዝቅኤል 45:19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ካህኑ የኃጢአት መባ ሆኖ ከቀረበው ደም የተወሰነውን ወስዶ በቤተ መቅደሱ መቃን፣+ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን አራት ማዕዘኖችና በውስጠኛው ግቢ በር መቃን ላይ ያድርግ።
-