ሕዝቅኤል 3:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ስለዚህ ተነስቼ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሄድኩ፤ እነሆም በኬባር ወንዝ+ አጠገብ ያየሁትን ክብር የሚመስል የይሖዋ ክብር በዚያ ነበር፤+ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ። ሕዝቅኤል 8:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከዚያም እጅ የሚመስል ነገር ዘርግቶ የራስ ፀጉሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል ይዞ ወሰደኝ፤ አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ቅናት የሚቀሰቅሰው የቅናት ጣዖት ምልክት* ወደቆመበት+ በሰሜን ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው ግቢ በር+ አመጣኝ። 4 እነሆም፣ በሸለቋማው ሜዳ አይቼው የነበረውን የሚመስል የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበር።+ ሕዝቅኤል 11:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 በዚህ ጊዜ ኪሩቦቹ ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘረጉ፤ መንኮራኩሮቹም* በአጠገባቸው ነበሩ፤+ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ነበር።+
3 ከዚያም እጅ የሚመስል ነገር ዘርግቶ የራስ ፀጉሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል ይዞ ወሰደኝ፤ አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ቅናት የሚቀሰቅሰው የቅናት ጣዖት ምልክት* ወደቆመበት+ በሰሜን ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው ግቢ በር+ አመጣኝ። 4 እነሆም፣ በሸለቋማው ሜዳ አይቼው የነበረውን የሚመስል የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበር።+