ኢዩኤል 2:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “በጽዮን ቀንደ መለከት ንፉ!+ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ ቀረርቶ አሰሙ። የአገሪቱ* ነዋሪዎች በሙሉ ይንቀጥቀጡ፤የይሖዋ ቀን ቀርቧልና!+ ቀኑ ደፍ ላይ ነው! ሶፎንያስ 1:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ታላቁ የይሖዋ ቀን ቅርብ ነው!+ ቅርብ ነው፤ ደግሞም በፍጥነት እየቀረበ ነው!*+ የይሖዋ ቀን ድምፅ አስፈሪ* ነው።+ በዚያ ተዋጊው ይጮኻል።+