-
ኤርምያስ 28:1-4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
28 በዚያው ዓመት፣ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ፣ በአራተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ የገባኦን+ ሰው የሆነው የአዙር ልጅ ነቢዩ ሃናንያህ፣ በይሖዋ ቤት ውስጥ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦ 2 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁ።+ 3 በሁለት ዓመት* ጊዜ ውስጥ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ከዚህ ስፍራ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን የይሖዋን ቤት ዕቃዎች ሁሉ ወደዚህ ቦታ መልሼ አመጣለሁ።’”+ 4 “‘የኢዮዓቄምን+ ልጅ፣ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን+ እንዲሁም ወደ ባቢሎን በግዞት የተወሰዱትን የይሁዳ ሰዎች ሁሉ+ ወደዚህ ቦታ መልሼ አመጣለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።’”
-