30 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወገኖችህ በየግድግዳው ሥርና በየቤቱ በራፍ ላይ ሆነው እርስ በርሳቸው ስለ አንተ ይነጋገራሉ።+ አንዱ ሌላውን፣ እያንዳንዱም ወንድሙን፣ ‘ና፣ ከይሖዋ የመጣውን ቃል እንስማ’ ይለዋል። 31 እንደ ሕዝቤ በፊትህ ለመቀመጥ ተሰብስበው ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ቃልህን ይሰማሉ፤ ሆኖም በተግባር አያውሉትም።+ በአፋቸው ይሸነግሉሃልና፤ ልባቸው ግን አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይስገበገባል።