18 በዚያ ቀን ይሖዋ ጌጦቻቸውን ሁሉ ይነጥቃል፦
አልቦውን፣ የፀጉር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን ጌጥ፣+
19 የጆሮ ጉትቻውን፣ አምባሩን፣ መከናነቢያውን፣
20 የራስ መሸፈኛውን፣ የሰንሰለት አልቦውን፣ ጌጠኛውን መቀነት፣
የሽቶ ዕቃውን፣ ክታቡን፣
21 የጣት ቀለበቱን፣ የአፍንጫ ቀለበቱን፣
22 የክት ልብሱን፣ መደረቢያውን፣ ካባውን፣ የእጅ ቦርሳውን፣
23 የእጅ መስተዋቱን፣+ የበፍታ ልብሶቹን፣
ጥምጥሙንና መከናነቢያውን ይወስድባቸዋል።