ሕዝቅኤል 23:46, 47 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 46 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘መቀጣጫ ያደርጋቸውና ለብዝበዛ ይዳርጋቸው ዘንድ በእነሱ ላይ ብዙ ሠራዊት ይሰበሰባል።+ 47 ሠራዊቱ ድንጋይ ይወረውርባቸዋል፤+ በሰይፉም ይቆራርጣቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ይገድላል፤+ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላል።+ ዕንባቆም 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እነሆ፣ ጨካኝና ፈጣን የሆነውን ብሔር ይኸውምከለዳውያንን አስነሳለሁና።+ የእነሱ ያልሆኑ ቤቶችን ለመውረስ፣ሰፋፊ የምድር ክፍሎችን ይወራሉ።+
46 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘መቀጣጫ ያደርጋቸውና ለብዝበዛ ይዳርጋቸው ዘንድ በእነሱ ላይ ብዙ ሠራዊት ይሰበሰባል።+ 47 ሠራዊቱ ድንጋይ ይወረውርባቸዋል፤+ በሰይፉም ይቆራርጣቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ይገድላል፤+ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላል።+