22 “ስለዚህ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ እርምጃ የምወስደው ለእናንተ ብዬ ሳይሆን በሄዳችሁባቸው ብሔራት መካከል ላረከሳችሁት ቅዱስ ስሜ ስል ነው።”’+ 23 ‘በብሔራት መካከል የረከሰውን፣ ይኸውም በእነሱ መካከል ያረከሳችሁትን ታላቅ ስሜን በእርግጥ እቀድሰዋለሁ፤+ ዓይኖቻቸው እያዩ በመካከላችሁ በምቀደስበት ጊዜ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ብሔራት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+