2 “‘ስለዚህ እነሆ፣ አሞናውያን በሚኖሩባት በራባ+ ላይ
የጦርነት ማስጠንቀቂያ ድምፅ የማሰማበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።
‘የፍርስራሽ ቁልል ትሆናለች፤
በእሷም ሥር ያሉት ከተሞች በእሳት ይቃጠላሉ።’
‘እስራኤልም የቀሙትን መልሶ በእጁ ያስገባል’+ ይላል ይሖዋ።
3 ‘ሃሽቦን ሆይ፣ ጋይ ስለወደመች ዋይ ዋይ በዪ!
በራባ ሥር ያላችሁ ከተሞች ሆይ፣ ጩኹ።
ማቅ ልበሱ።
ማልካም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር
በግዞት ስለሚወሰድ+
ከድንጋይ በተሠራ የእንስሳት ማጎሪያ ውስጥ ወዲያ ወዲህ እያላችሁ አልቅሱ።