12 “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ጢሮስ ንጉሥ ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“አንተ ጥበብ የተሞላህና+ ፍጹም ውበት የተላበስክ+
የፍጽምና ተምሳሌት ነበርክ።
13 በአምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ነበርክ።
በከበሩ ድንጋዮች ሁሉ
ይኸውም በሩቢ፣ በቶጳዝዮን፣ በኢያስጲድ፣ በክርስቲሎቤ፣ በኦኒክስ፣ በጄድ፣ በሰንፔር፣ በበሉርና+ በመረግድ አጊጠህ ነበር፤
እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች የተሰኩባቸው ማቀፊያዎችም ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ።
በተፈጠርክበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።