ዘፍጥረት 25:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 በመሆኑም ኤሳው ያዕቆብን “ቶሎ በል እባክህ፣ በጣም ስለደከመኝ* ከዚያ ከቀዩ ወጥ የተወሰነ* ስጠኝ!” አለው። ስሙ ኤዶም*+ የተባለውም በዚህ የተነሳ ነው። ኢሳይያስ 34:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “ሰይፌ በሰማያት በደም ትርሳለችና።+ በኤዶም ይኸውም እንዲጠፋፍርድ ባስተላለፍኩበት ሕዝብ ላይ ትወርዳለች።+ ሕዝቅኤል 25:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ኤዶም በቂም በቀል ተነሳስቶ በይሁዳ ቤት ላይ እርምጃ ወስዷል፤ ደግሞም እነሱን በመበቀል ከፍተኛ በደል ፈጽሟል፤+ 13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ።+ ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ አሞጽ 1:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የኤዶም ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም የገዛ ወንድሙን በሰይፍ አሳዷል፤+ምሕረት ለማሳየትም እንቢተኛ ሆኗል፤በቁጣው ያላንዳች ፋታ ይዘነጣጥላቸዋል፤አሁንም ቢሆን በእነሱ ላይ ቁጣው አልበረደም።+ አብድዩ 1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 1 የአብድዩ* ራእይ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦+ “ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምተናል፤በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦ ‘ተነሱ፤ እሷን ለመውጋት እንዘጋጅ።’”+ ሚልክያስ 1:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 “ኤዶም* ‘ተደምስሰናል፤ ሆኖም ተመልሰን የፈራረሱትን ዳግመኛ እንገነባለን’ ቢልም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሱ ይገነባሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ቦታዎቹ “የክፋት ምድር፣” እነሱ ደግሞ “ይሖዋ ለዘላለም ያወገዘው ሕዝብ” ተብለው ይጠራሉ።+
30 በመሆኑም ኤሳው ያዕቆብን “ቶሎ በል እባክህ፣ በጣም ስለደከመኝ* ከዚያ ከቀዩ ወጥ የተወሰነ* ስጠኝ!” አለው። ስሙ ኤዶም*+ የተባለውም በዚህ የተነሳ ነው።
12 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ኤዶም በቂም በቀል ተነሳስቶ በይሁዳ ቤት ላይ እርምጃ ወስዷል፤ ደግሞም እነሱን በመበቀል ከፍተኛ በደል ፈጽሟል፤+ 13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ።+ ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።+
11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የኤዶም ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም የገዛ ወንድሙን በሰይፍ አሳዷል፤+ምሕረት ለማሳየትም እንቢተኛ ሆኗል፤በቁጣው ያላንዳች ፋታ ይዘነጣጥላቸዋል፤አሁንም ቢሆን በእነሱ ላይ ቁጣው አልበረደም።+
1 የአብድዩ* ራእይ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦+ “ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምተናል፤በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦ ‘ተነሱ፤ እሷን ለመውጋት እንዘጋጅ።’”+
4 “ኤዶም* ‘ተደምስሰናል፤ ሆኖም ተመልሰን የፈራረሱትን ዳግመኛ እንገነባለን’ ቢልም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሱ ይገነባሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ቦታዎቹ “የክፋት ምድር፣” እነሱ ደግሞ “ይሖዋ ለዘላለም ያወገዘው ሕዝብ” ተብለው ይጠራሉ።+