-
ዳንኤል 2:40-42አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
40 “አራተኛው መንግሥት ደግሞ እንደ ብረት የጠነከረ ይሆናል።+ ብረት ሁሉንም ነገር እንደሚሰባብርና እንደሚፈጭ ሁሉ፣ እሱም እንደሚያደቅ ብረት እነዚህን መንግሥታት ሁሉ ይሰባብራቸዋል፤ ደግሞም ያደቅቃቸዋል።+
41 “እግሮቹና ጣቶቹ ከፊሉ ሸክላ፣ ከፊሉ ደግሞ ብረት ሆነው እንዳየህ ሁሉ መንግሥቱም የተከፋፈለ ይሆናል፤ ሆኖም ብረቱና የሸክላ ጭቃው ተደባልቆ እንዳየህ ሁሉ በተወሰነ መጠን የብረት ጥንካሬ ይኖረዋል። 42 የእግሮቹ ጣቶች ከፊሉ ብረት፣ ከፊሉ ሸክላ እንደሆኑ ሁሉ ይህም መንግሥት በከፊል ብርቱ፣ በከፊል ደግሞ ደካማ ይሆናል።
-