16 የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ በነገሠ በ17ኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓታም ልጅ አካዝ+ ነገሠ። 2 አካዝ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 20 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በአምላኩ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አላደረገም።+ 3 ከዚህ ይልቅ የእስራኤልን ነገሥታት መንገድ ተከተለ፤+ ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሙ የነበረውን አስጸያፊ ድርጊት በመከተል+ የገዛ ልጁን እንኳ ሳይቀር ለእሳት አሳልፎ ሰጠ።+