ኢሳይያስ 59:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ከእኛ ራቀ፤ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም። ብርሃን ይሆናል ብለን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ሆኖም ጨለማ ሆነ፤ጸዳልን ተጠባበቅን፤ ሆኖም በጨለማ እንመላለሳለን።+ 10 ልክ እንደ ዓይነ ስውራን ቅጥሩን እየዳበስን እንሄዳለን፤ዓይን እንደሌላቸው ሰዎች እንደናበራለን።+ በምሽት ጨለማ እንደሚሆነው በቀትር ብርሃን እንሰናከላለን፤በብርቱ ሰዎች መካከል እንደ ሙታን ነን። አሞጽ 8:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ‘በዚያ ቀን’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣‘ፀሐይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ብሩህ በሆነ ቀንም ምድሪቱን አጨልማለሁ።+
9 ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ከእኛ ራቀ፤ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም። ብርሃን ይሆናል ብለን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ሆኖም ጨለማ ሆነ፤ጸዳልን ተጠባበቅን፤ ሆኖም በጨለማ እንመላለሳለን።+ 10 ልክ እንደ ዓይነ ስውራን ቅጥሩን እየዳበስን እንሄዳለን፤ዓይን እንደሌላቸው ሰዎች እንደናበራለን።+ በምሽት ጨለማ እንደሚሆነው በቀትር ብርሃን እንሰናከላለን፤በብርቱ ሰዎች መካከል እንደ ሙታን ነን።