ዘኁልቁ 14:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ የሚንቀኝ እስከ መቼ ነው?+ በመካከላቸው ይህን ሁሉ ተአምራዊ ምልክት እያሳየሁ የማያምኑብኝስ እስከ መቼ ነው?+ 12 እንግዲህ በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ ደግሞም እደመስሳቸዋለሁ፤ አንተን ግን ከእነሱ ይልቅ ታላቅና ኃያል ብሔር አደርግሃለሁ።”+ ዘኁልቁ 16:46 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 46 ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “የዕጣን ማጨሻ ውሰድና ከመሠዊያው ላይ እሳት አድርግበት፤+ በላዩም ላይ ዕጣን ጨምርበት፤ ፈጥነህም ወደ ማኅበረሰቡ በመሄድ አስተሰርይላቸው፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ተቆጥቷል። መቅሰፍቱ ጀምሯል!” ዘኁልቁ 25:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 እስራኤላውያን በሺቲም+ ይኖሩ በነበረበት ጊዜ ሕዝቡ ከሞዓብ ሴቶች ጋር የፆታ ብልግና መፈጸም ጀመረ።+ ዘኁልቁ 25:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች 24,000 ነበሩ።+
11 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ የሚንቀኝ እስከ መቼ ነው?+ በመካከላቸው ይህን ሁሉ ተአምራዊ ምልክት እያሳየሁ የማያምኑብኝስ እስከ መቼ ነው?+ 12 እንግዲህ በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ ደግሞም እደመስሳቸዋለሁ፤ አንተን ግን ከእነሱ ይልቅ ታላቅና ኃያል ብሔር አደርግሃለሁ።”+
46 ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “የዕጣን ማጨሻ ውሰድና ከመሠዊያው ላይ እሳት አድርግበት፤+ በላዩም ላይ ዕጣን ጨምርበት፤ ፈጥነህም ወደ ማኅበረሰቡ በመሄድ አስተሰርይላቸው፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ተቆጥቷል። መቅሰፍቱ ጀምሯል!”