5 የከለዳውያን ሠራዊት ግን አሳደዳቸው፤ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት።+ ከያዙት በኋላ በሃማት+ ምድር በሪብላ+ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነጾር አመጡት፤ እሱም በዚያ ፈረደበት። 6 የባቢሎን ንጉሥ በሪብላ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አሳረዳቸው፤ በተጨማሪም የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ታላላቅ ሰዎች ሁሉ አሳረደ።+ 7 የሴዴቅያስንም ዓይን አሳወረ፤ ከዚያም ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በመዳብ የእግር ብረት አሰረው።+