18 በመጨረሻም ምናሴ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቤቱም በሚገኘው የአትክልት ስፍራ ይኸውም በዑዛ የአትክልት ስፍራ ተቀበረ፤+ ልጁም አምዖን በእሱ ምትክ ነገሠ።
19 አምዖን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሁለት ዓመት ገዛ።+ እናቱ ሜሹሌሜት ትባል ነበር፤ እሷም የዮጥባ ሰው የሆነው የሃሩጽ ልጅ ነበረች። 20 አምዖን አባቱ ምናሴ እንዳደረገው በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+