2 ነገሥት 22:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ኢዮስያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ31 ዓመት ገዛ።+ እናቱ ይዲዳ ትባል ነበር፤ እሷም የቦጽቃት+ ሰው የሆነው የአዳያህ ልጅ ነበረች። 2 ኢዮስያስም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤+ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አላለም። ኤርምያስ 1:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የይሁዳ ንጉሥ የአምዖን+ ልጅ ኢዮስያስ+ በነገሠ በ13ኛው ዓመት የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ።
22 ኢዮስያስ+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ31 ዓመት ገዛ።+ እናቱ ይዲዳ ትባል ነበር፤ እሷም የቦጽቃት+ ሰው የሆነው የአዳያህ ልጅ ነበረች። 2 ኢዮስያስም በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤+ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አላለም።