የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 126:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 126 ይሖዋ የጽዮንን ምርኮኞች መልሶ በሰበሰበ ጊዜ፣+

      ሕልም የምናይ መስሎን ነበር።

  • ኤርምያስ 23:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 “ከዚያም የቀሩትን በጎቼን ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደ መሰማሪያቸውም መልሼ አመጣቸዋለሁ፤+ እነሱም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ደግሞም ይበዛሉ።+

  • ሕዝቅኤል 39:25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምርኮ የተወሰዱትን የያዕቆብ ወገኖች እመልሳለሁ፤+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤+ የስሜንም ቅድስና አስከብራለሁ።*+

  • አሞጽ 9:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+

      እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+

      የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+

      አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+

  • ሚክያስ 2:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ያዕቆብ ሆይ፣ ሁላችሁንም በእርግጥ እሰበስባለሁ፤

      ከእስራኤል የቀሩትን ያላንዳች ጥርጥር አንድ ላይ እሰበስባለሁ።+

      በጉረኖ ውስጥ እንዳለ በግ፣

      በግጦሽ መስክ ላይ እንዳለም መንጋ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤+

      ቦታውም በሕዝብ ሁካታ ይሞላል።’+

  • ሚክያስ 4:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት

      ተንፈራገጪ፤ አቃስቺም፤

      አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትሰፍሪያለሽና።

      እስከ ባቢሎን ድረስ ትሄጃለሽ፤+

      በዚያም ይታደግሻል፤+

      በዚያ ይሖዋ ከጠላቶችሽ እጅ ይዋጅሻል።+

  • ሶፎንያስ 3:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 በዚያን ጊዜ መልሼ አመጣችኋለሁ፤

      አዎ፣ በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ።

      ተማርከው የተወሰዱባችሁን ሰዎች በፊታችሁ መልሼ በምሰበስብበት ጊዜ+

      በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ዝና* እንድታተርፉና እንድትወደሱ አደርጋለሁና”+ ይላል ይሖዋ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ