-
ሐጌ 1:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ብዙ ዘር ዘራችሁ፤ የምትሰበስቡት ግን ጥቂት ነው።+ ትበላላችሁ፤ ሆኖም አትጠግቡም። ትጠጣላችሁ፤ ሆኖም አትረኩም። ትለብሳላችሁ፤ የሚሞቀው ሰው ግን የለም። ተቀጥሮ የሚሠራው ደሞዙን ብዙ ቀዳዳዎች ባሉት ከረጢት ውስጥ ያስቀምጣል።’”
-
-
ዘካርያስ 8:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ከእነዚያ ቀናት በፊት ለሰውም ሆነ ለእንስሳ የሚከፈል ደሞዝ አልነበረምና፤+ ደግሞም ከጠላት የተነሳ በሰላም መግባትና መውጣት አይቻልም ነበር፤ ሰው ሁሉ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ አድርጌ ነበርና።’
-