ዘሌዋውያን 19:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “‘አትስረቁ፤+ አታታሉ፤+ አንዳችሁ በሌላው ላይ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት አትፈጽሙ። ምሳሌ 12:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤+ሐሰተኛ ምላስ ግን የሚቆየው ለቅጽበት ብቻ ነው።+ ኤፌሶን 4:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ስለዚህ አሁን አታላይነትን ስላስወገዳችሁ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ* ጋር እውነትን ተነጋገሩ፤+ ምክንያቱም ሁላችንም የአንድ አካል ክፍሎች ነን።+