13 ከሕዝቡ ላይ የካህናቱን ድርሻ በሚቀበሉበት ጊዜ እንዲህ ያደርጉ ነበር፦+ ማንኛውም ሰው መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለው ሹካ ይዞ ይመጣና 14 ሹካውን ወደ ሰታቴው ወይም ወደ ምንቸቱ ወይም ወደ አፍላሉ ወይም ወደ ባለ አንድ ጆሮው ድስት ይከተዋል። መንሹ ይዞ የሚወጣውንም ካህኑ ለራሱ ይወስድ ነበር። ወደ ሴሎ በሚመጡት እስራኤላውያን ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጉ ነበር።