-
ዘሌዋውያን 26:14-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 “‘ይሁን እንጂ የማትሰሙኝ ወይም እነዚህን ትእዛዛት በሙሉ የማትፈጽሙ ከሆነ+ 15 እንዲሁም ደንቦቼን ችላ የምትሉና+ ትእዛዛቴን በሙሉ ላለመፈጸም ድንጋጌዎቼን የምትጸየፉ፣* ቃል ኪዳኔንም የምታፈርሱ ከሆነ+ 16 እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፦ ዓይናችሁ እንዲጠፋና ሕይወታችሁ* እንዲመነምን የሚያደርግ የሳንባ ነቀርሳና ኃይለኛ ትኩሳት በእናንተ ላይ በማምጣት በጭንቀት እቀጣችኋለሁ። ዘራችሁን የምትዘሩት እንዲሁ በከንቱ ይሆናል፤ ምክንያቱም የሚበሉት ጠላቶቻችሁ ናቸው።+ 17 እኔም በእርግጥ ፊቴን አጠቁርባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ድል ያደርጓችኋል፤+ የሚጠሏችሁም ሰዎች ይረግጧችኋል፤+ እንዲሁም ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።+
-
-
ዘዳግም 28:15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 “እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች በሙሉ በጥንቃቄ የማትፈጽምና የአምላክህን የይሖዋን ቃል የማትሰማ ከሆነ ግን እነዚህ ሁሉ እርግማኖች ይወርዱብሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦+
-