-
ሉቃስ 6:47-49አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
47 ወደ እኔ የሚመጣ፣ ቃሌን የሚሰማና የሚያደርግ ሁሉ ከማን ጋር እንደሚመሳሰል ልንገራችሁ፦+ 48 ቤት ለመሥራት በጥልቀት ቆፍሮ በዓለት ላይ መሠረቱን ከጣለ ሰው ጋር ይመሳሰላል። በኋላም ጎርፍ በመጣ ጊዜ ወንዙ ቤቱን በኃይል መታው፤ ሆኖም ቤቱ በደንብ ስለተገነባ ሊያነቃንቀው አልቻለም።+ 49 በሌላ በኩል ደግሞ ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ሰው+ ሁሉ መሠረት ሳይጥል፣ በአፈር ላይ ቤት ከሠራ ሰው ጋር ይመሳሰላል። ወንዙም ቤቱን በኃይል መታው፤ ወዲያውም ተደረመሰ፤ እንዳልነበረም ሆነ።”
-