-
ማርቆስ 2:15-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 በኋላም በሌዊ ቤት ተቀምጦ እየበላ ነበር፤ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኃጢአተኞችም ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እየበሉ ነበር። ከእነሱም መካከል ብዙዎቹ እሱን መከተል ጀምረው ነበር።+ 16 ሆኖም ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ ጸሐፍት ከኃጢአተኞችና ከቀረጥ ሰብሳቢዎች ጋር ሲበላ ባዩ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “እንዴት ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር ይበላል?” አሏቸው። 17 ኢየሱስ ይህን ሲሰማ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ልጠራ ነው” አላቸው።+
-
-
ሉቃስ 5:29-32አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 ከዚያም ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ በግብዣውም ላይ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ሰዎች ከእነሱ ጋር ይበሉ ነበር።+ 30 ፈሪሳውያንና ከእነሱ ወገን የሆኑ ጸሐፍት ይህን ባዩ ጊዜ “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የምትበሉትና የምትጠጡት ለምንድን ነው?” በማለት በደቀ መዛሙርቱ ላይ ማጉረምረም ጀመሩ።+ 31 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።+ 32 እኔ የመጣሁት ኃጢአተኞች ንስሐ እንዲገቡ ለመጥራት እንጂ ጻድቃንን ለመጥራት አይደለም።”+
-