18 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን የመጾም ልማድ ነበራቸው። ስለዚህም ወደ እሱ መጥተው “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ዘወትር ሲጾሙ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?” አሉት።+ 19 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው+ ከእነሱ ጋር እያለ ጓደኞቹ የሚጾሙበት ምን ምክንያት አለ? ሙሽራው አብሯቸው እስካለ ድረስ ሊጾሙ አይችሉም። 20 ሆኖም ሙሽራው ከእነሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤+ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።