-
ዘኁልቁ 27:16, 17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 “የሰው* ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነው ይሖዋ በማኅበረሰቡ ላይ አንድ ሰው ይሹም፤ 17 እሱም የይሖዋ ማኅበረሰብ እረኛ እንደሌላቸው በጎች እንዳይሆን በፊታቸው የሚወጣና የሚገባ እንዲሁም እነሱን መርቶ የሚያወጣና የሚያስገባ ይሆናል።”
-
-
1 ነገሥት 22:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 በመሆኑም ሚካያህ እንዲህ በማለት ተናገረ፦ “እስራኤላውያን ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበታትነው አያለሁ።+ ይሖዋም ‘እነዚህ ጌታ የላቸውም። እያንዳንዳቸው በሰላም ወደየቤታቸው ይመለሱ’ ብሏል።”
-
-
ሕዝቅኤል 34:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 በጎቹ እረኛ በማጣታቸው ተበታተኑ፤+ ተበታትነው ለዱር አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ።
-