-
የሐዋርያት ሥራ 4:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ+ እንዲህ አላቸው፦
“እናንተ የሕዝቡ ገዢዎችና ሽማግሌዎች፣
-
-
የሐዋርያት ሥራ 24:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 አገረ ገዢውም እንዲናገር በጭንቅላቱ ምልክት በሰጠው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፦
“ለብዙ ዓመታት ለዚህ ሕዝብ ፈራጅ ሆነህ ስታገለግል መቆየትህን አውቃለሁ፤ በመሆኑም ስለ ራሴ የመከላከያ መልስ የማቀርበው በደስታ ነው።+
-
-
የሐዋርያት ሥራ 25:23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ስለዚህ በማግስቱ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ክብር ደምቀው እንዲሁም በሻለቃዎችና በከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ታጅበው ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ ገቡ፤ ፊስጦስም ትእዛዝ በሰጠ ጊዜ ጳውሎስ እንዲቀርብ ተደረገ።
-
-
የሐዋርያት ሥራ 26:25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፦ “ክቡር ፊስጦስ ሆይ፣ አእምሮዬን እየሳትኩ አይደለም፤ እኔ እየተናገርኩ ያለሁት እውነተኛ እንዲሁም ከጤናማ አእምሮ የሚመነጭ ቃል ነው።
-