51 የመጣሁት በምድር ላይ ሰላም ለማስፈን ይመስላችኋል? በፍጹም አይደለም፤ እላችኋለሁ፣ የመጣሁት ሰላም ለማስፈን ሳይሆን ለመከፋፈል ነው።+ 52 ከአሁን ጀምሮ በአንድ ቤት ውስጥ እርስ በርስ የተከፋፈሉ አምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሦስቱ በሁለቱ ላይ ሁለቱ ደግሞ በሦስቱ ላይ ይነሳሉ። 53 አባት በልጁ፣ ልጅ በአባቱ፣ እናት በልጇ፣ ልጅ በእናቷ፣ አማት በምራቷ፣ ምራት በአማቷ ላይ በመነሳት እርስ በርስ ይከፋፈላሉ።”+