የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 12:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ፤ በሰባተኛውም ቀን ሌላ ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ። በእነዚህ ቀናት ምንም ዓይነት ሥራ መሠራት የለበትም።+ እያንዳንዱ ሰው* የሚበላውን ነገር ከማዘጋጀት ውጭ ሌላ ምንም ነገር አትሥሩ።

  • ዘዳግም 23:25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 25 “ወደ ባልንጀራህ የእህል ማሳ ከገባህ እሸት ቀጥፈህ መብላት ትችላለህ፤ ሆኖም የባልንጀራህን እህል በማጭድ ማጨድ የለብህም።+

  • ማርቆስ 2:23-28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 23 በሰንበት ቀን በእህል እርሻ መካከል እያለፈ ሳለ አብረውት ይሄዱ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር።+ 24 በመሆኑም ፈሪሳውያን “ተመልከት! በሰንበት ቀን በሕግ የተከለከለ ነገር የሚያደርጉት ለምንድን ነው?” አሉት። 25 እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ዳዊት የሚበላው ባጣ ጊዜ እንዲሁም እሱና አብረውት የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ነገር ፈጽሞ አላነበባችሁም?+ 26 ሊቀ ካህናት ስለሆነው ስለ አብያታር+ በሚናገረው ታሪክ ላይ ዳዊት ወደ አምላክ ቤት ገብቶ ከካህናት በቀር ማንም እንዲበላ ያልተፈቀደውን በአምላክ ፊት የቀረበ ኅብስት+ እንደበላና ከእሱ ጋር ለነበሩትም እንደሰጣቸው አላነበባችሁም?” 27 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰንበት ለሰው ተሰጠ እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም።+ 28 በመሆኑም የሰው ልጅ የሰንበትም እንኳ ጌታ ነው።”+

  • ሉቃስ 6:1-5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 በአንድ የሰንበት ቀን ኢየሱስ በእህል እርሻ መካከል እያለፈ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ እሸት ቀጥፈው በእጃቸው እያሹ+ ይበሉ ነበር።+ 2 በዚህ ጊዜ አንዳንድ ፈሪሳውያን “በሰንበት ቀን በሕግ የተከለከለ ነገር የምታደርጉት ለምንድን ነው?” አሏቸው።+ 3 ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ዳዊት እሱና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ነገር ፈጽሞ አላነበባችሁም?+ 4 ወደ አምላክ ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር ማንም እንዲበላው ያልተፈቀደውን በአምላክ ፊት የቀረበ ኅብስት ተቀብሎ እንደበላና ከእሱ ጋር ለነበሩት እንደሰጣቸው አላነበባችሁም?”+ 5 ከዚያም “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው” አላቸው።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ