የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማርቆስ 6:21-29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 ይሁንና ሄሮድስ በልደት ቀኑ+ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን፣ የጦር አዛዦቹንና በገሊላ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ራት በጋበዘ ጊዜ ሄሮድያዳ ምቹ አጋጣሚ ተፈጠረላት።+ 22 የሄሮድያዳ ልጅ ገብታ በመጨፈር ሄሮድስንና ከእሱ ጋር እየበሉ የነበሩትን አስደሰተቻቸው። ንጉሡም ልጅቷን “የፈለግሽውን ሁሉ ጠይቂኝ፣ እሰጥሻለሁ” አላት። 23 ደግሞም “እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ቢሆን የምትጠይቂኝን ሁሉ እሰጥሻለሁ” ሲል ማለላት። 24 እሷም ወደ እናቷ ሄዳ “ምን ብጠይቀው ይሻላል?” አለቻት። እናቷም “የአጥማቂው ዮሐንስን ራስ ጠይቂው” አለቻት። 25 ወዲያውም ወደ ንጉሡ ፈጥና በመግባት “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አሁኑኑ በሳህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” ስትል ጠየቀችው።+ 26 ንጉሡ በዚህ እጅግ ቢያዝንም ስለገባው መሐላና ስለ እንግዶቹ ሲል እንቢ ሊላት አልፈለገም። 27 ከዚያም ንጉሡ ጠባቂውን ወዲያው ልኮ የዮሐንስን ራስ እንዲያመጣ አዘዘው። ጠባቂውም ሄዶ ወህኒ ቤት ውስጥ ራሱን ቆረጠው፤ 28 ራሱንም በሳህን ይዞ መጣ። ከዚያም ለልጅቷ ሰጣት፤ ልጅቷም ለእናቷ ሰጠቻት። 29 ደቀ መዛሙርቱም ይህን በሰሙ ጊዜ መጥተው አስከሬኑን በመውሰድ በመቃብር አኖሩት።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ