-
ማርቆስ 7:25-30አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ወዲያውም፣ ትንሽ ልጇ በርኩስ መንፈስ የተያዘችባት አንዲት ሴት ስለ እሱ ሰምታ መጣችና እግሩ ላይ ወደቀች።+ 26 ሴትየዋ ግሪካዊት፣ በዜግነት* ደግሞ ሲሮፊንቃዊት ነበረች፤ እሷም ጋኔኑን ከልጇ እንዲያስወጣላት ወተወተችው። 27 እሱ ግን “የልጆችን ዳቦ ወስዶ ለቡችሎች መጣል ተገቢ ስላልሆነ መጀመሪያ ልጆቹ ይጥገቡ” አላት።+ 28 ሆኖም ሴትየዋ መልሳ “አዎ ጌታዬ፣ ቡችሎችም እኮ ከገበታ በታች ሆነው ከልጆች የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለችው። 29 በዚህ ጊዜ “ሂጂ፤ እንዲህ ስላልሽ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቷል” አላት።+ 30 እሷም ወደ ቤቷ ስትመለስ ልጇ አልጋ ላይ ተኝታ፣ ጋኔኑም ወጥቶላት አገኘቻት።+
-