የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 16:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 መቃብር* ውስጥ አትተወኝምና።*+

      ታማኝ አገልጋይህ ጉድጓድ እንዲያይ* አትፈቅድም።+

  • ኢሳይያስ 53:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ስለዚህ ከብዙዎች ጋር ድርሻውን እሰጠዋለሁ፤

      ምርኮውን ከኃያላን ጋር ይካፈላል፤

      ሕይወቱን* እስከ ሞት ድረስ አፍስሷልና፤+

      ከሕግ ተላላፊዎችም ጋር ተቆጥሯል፤+

      የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸክሟል፤+

      ስለ ሕግ ተላላፊዎችም ማልዷል።+

  • ማቴዎስ 17:22, 23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 በገሊላ ተሰብስበው ሳሉ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የሰውን ልጅ ለሰዎች አሳልፈው ይሰጡታል፤+ 23 እነሱም ይገድሉታል፤ እሱም በሦስተኛው ቀን ይነሳል።”+ ደቀ መዛሙርቱም በጣም አዘኑ።

  • ማቴዎስ 20:18, 19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 “እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት አልፎ ይሰጣል። እነሱም ሞት ይፈርዱበታል፤+ 19 እንዲሁም እንዲያፌዙበት፣ እንዲገርፉትና በእንጨት ላይ እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤+ እሱም በሦስተኛው ቀን ይነሳል።”+

  • ማርቆስ 8:31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 በተጨማሪም የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበሉ እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት ተቀባይነት ማጣቱ ብሎም መገደሉና+ ከሦስት ቀን በኋላ መነሳቱ+ እንደማይቀር ያስተምራቸው ጀመር።

  • ሉቃስ 9:22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 ቀጥሎም “የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበሉ፣ እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት ተቀባይነት ማጣቱ ብሎም መገደሉና+ በሦስተኛው ቀን መነሳቱ+ አይቀርም” አላቸው።

  • ሉቃስ 24:46
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 46 እንዲህም አላቸው፦ “እንደሚከተለው ተብሎ ተጽፏል፤ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሳል፤+

  • 1 ቆሮንቶስ 15:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 እኔ የተቀበልኩትን ከሁሉ በላይ የሆነውን ነገር ለእናንተ አስተላልፌአለሁና፤ ይኸውም ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤+ 4 ደግሞም ተቀበረ፤+ ቅዱሳን መጻሕፍት+ እንደሚሉትም በሦስተኛው ቀን+ ተነሳ፤+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ