-
ማርቆስ 10:35-40አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
35 ሁለቱ የዘብዴዎስ ልጆች+ ያዕቆብና ዮሐንስ ወደ እሱ ቀርበው “መምህር፣ የምንለምንህን ማንኛውንም ነገር እንድታደርግልን እንፈልጋለን” አሉት።+ 36 እሱም “ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። 37 እነሱም “በክብር ቦታህ ላይ ስትቀመጥ አንዳችን በቀኝህ፣ አንዳችን ደግሞ በግራህ እንድንቀመጥ ፍቀድልን” ሲሉ መለሱለት።+ 38 ኢየሱስ ግን “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ እየጠጣሁት ያለውን ጽዋ ልትጠጡ ወይም እኔ እየተጠመቅኩት ያለውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁ?” አላቸው።+ 39 እነሱም “እንችላለን” አሉት። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ እየጠጣሁት ያለውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔ እየተጠመቅኩት ያለውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ።+ 40 በቀኜ ወይም በግራዬ መቀመጥ ግን ለተዘጋጀላቸው የሚሰጥ እንጂ በእኔ ፈቃድ የሚሆን አይደለም።”
-