-
ሉቃስ 3:7-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 በመሆኑም ዮሐንስ በእሱ እጅ ለመጠመቅ የሚመጡትን ሰዎች እንዲህ ይላቸው ነበር፦ “እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ያስጠነቀቃችሁ ማን ነው?+ 8 እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ። ‘እኛ እኮ አባታችን አብርሃም ነው’ እያላችሁ ራሳችሁን አታጽናኑ። አምላክ ለአብርሃም ከእነዚህ ድንጋዮች ልጆች ማስነሳት እንደማይሳነው ልነግራችሁ እወዳለሁ። 9 እንዲያውም መጥረቢያው ዛፎቹ ሥር ተቀምጧል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ እሳት ውስጥ ይጣላል።”+
-
-
ሉቃስ 21:23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!+ ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቁጣ ይመጣል።
-