-
ማቴዎስ 3:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 መጥረቢያው ዛፎቹ ሥር ተቀምጧል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ እሳት ውስጥ ይጣላል።+
-
-
ማርቆስ 11:13, 14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ቅጠሏ የለመለመ አንዲት የበለስ ዛፍ ከሩቅ አየና ምናልባት ፍሬ ይገኝባት እንደሆነ ለማየት ሄደ። ወደ እሷ በቀረበ ጊዜ ግን በለስ የሚያፈራበት ወቅት ስላልነበረ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። 14 ስለዚህ ኢየሱስ ዛፏን “ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ” አላት።+ ይህን ሲናገርም ደቀ መዛሙርቱ ይሰሙት ነበር።
-