-
ዘፍጥረት 38:7, 8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 ይሁንና የይሁዳ የበኩር ልጅ ኤር ይሖዋ ያዘነበት ሰው ነበር፤ በመሆኑም ይሖዋ በሞት ቀሰፈው። 8 በዚህ የተነሳ ይሁዳ ኦናንን “ከወንድምህ ሚስት ጋር ግንኙነት በመፈጸም የዋርሳነት ግዴታህን ተወጣ፤ ለወንድምህም ዘር ተካለት” አለው።+
-
-
ሩት 1:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ናኦሚ ግን እንዲህ አለቻቸው፦ “ልጆቼ፣ ተመለሱ። ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ለእናንተ ባሎች ሊሆኑ የሚችሉ ወንዶች ልጆች አሁንም ልወልድ የምችል ይመስላችኋል?+
-
-
ሩት 3:13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ዛሬ እዚሁ እደሪ፤ ሲነጋም ሰውዬው የሚቤዥሽ ከሆነ፣ መልካም! እሱ ይቤዥሽ።+ ሊቤዥሽ የማይፈልግ ከሆነ ግን ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ እኔው ራሴ እቤዥሻለሁ። እስከ ማለዳ ድረስ ግን እዚሁ ተኚ።”
-