ዘሌዋውያን 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “‘የሕዝብህን ልጆች አትበቀል፤+ በእነሱም ላይ ቂም አትያዝ፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። ማርቆስ 12:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ሁለተኛው ደግሞ ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’ የሚል ነው።+ ከእነዚህ የሚበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለም።” ሉቃስ 10:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው። ቆላስይስ 3:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ይሁንና በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ላይ ፍቅርን ልበሱ፤+ ፍቅር ፍጹም የሆነ የአንድነት ማሰሪያ ነውና።+ ያዕቆብ 2:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እንግዲያው በቅዱስ መጽሐፉ መሠረት “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ የሚለውን ንጉሣዊ ሕግ ተግባራዊ የምታደርጉ ከሆነ መልካም እያደረጋችሁ ነው። 1 ጴጥሮስ 1:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ራሳችሁን* ስላነጻችሁ ግብዝነት የሌለበት የወንድማማች መዋደድ አላችሁ፤+ በመሆኑም እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ።+
27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው።